የአመራርና የባለድርሻ አካል ተሳትፎ

የቡድን ምስረታ የድርጊት ዕቅድ

ዓላማ: ይህ ቴምፕሌት የመሰረታዊ የቡድን ባህሪ ጅማሪ ነው፡፡ ቴምፕሌቱ ለእርስዎና ለቡድንዎ የቡድን ምስረታ ደረጃዎችን እንዴት ውጤታማ በሆነ መልኩ እንደምታልፉ በንቃት የምታቅዱበት ህያው ሰነድ ነው፡፡ ሰነዱ ከመጀመሪያው አንስቶ ራዕይዎን እና አሰራርዎን እንዲያዘጋጁ ይረዳዎታል፡፡

እንዴት እንደሚጠቀሙት: ይህን “በምስረታ” ደረጃ ላይ ከአዲሱ ቡድንዎ ጋር ሆነው ይሙሉት እና በየጥቂት ወራት ውስጥ ተመልሰው ይመልከቱት፡፡ ይህ አሰራር አስበውበት ከፍተኛ ፈጻሚ ቡድን እንዲመሰርቱ ይረዳዎታል፡፡

ቴምፕሌት: የቡድን ምስረታ የድርጊት ዕቅድ

ምሳሌ

ዋና ዋና ነጥቦች  

ዝርዝሮች  

የስራ ድርሻ ወይም ኃላፊነት

ዋና ዋና ኃላፊነት

መሰረታችን  

(የ”ምስረታ” ደረጃ)

የቡድን መሪ

ድርጅታዊ መዋቅር ማዘጋጀት

ተልዕኳችን

ያለነው ለምንድን ነው? (ምሳ፡ ንጹህ ማብሰያን ሀዋሳ ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች ተደራሽ ለማድረግ)

 

 

የስኬት ራዕያችን

በ1 ዓመት ውስጥ ድርጅቱ ሲያሳካ ምን ይመስላል? (ምሳ፡ 500 ምድጃዎችን በመሸጥ በከፍተኛ የደንበኛ አገልግሎት መልካም ስም እናገኛለን)፡፡

 

 

ዋና ዋና ግቦች

በቀጣዮቹ 3 ወራት ውስጥ (ከ2-3 ዓላማ ተኮር፣ ሊለኩ የሚችሉ ግቦችን ይዘርዝሩ)

 

 

ለ: በ “ግጭት” እና “አሰራር ማዘጋጀት” ላይ መምራት)

ሁኔታዎች  

የድርጊት ዕቅድ  

እንዴት ግንኙነት እንደምናደርግ

(ለምሳሌ፡ በእያንዳንዱ ቀን ጠዋት ማረጋገጥ (10 ደቂቃዎች)፣ ለአስቸኳይ ወቅታዊ መረጃዎች ስልክ መደወል፣ ለመመለስ ሳይሆን ለመረዳት ስንል ለማዳመጥ ዝግጁ ነን፡፡)

አለመግባባቶች እንዴት እንደሚፈቱ

በምንጋጭበት ወቅት እንዲህ እናደርጋለን… (ለምሳሌ፡ 1. የሌላኛውን ሰው እይታ እንቀበላለን፡፡ 2. በግለሰቡ ላይ ሳይሆን በችግሩ ላይ እናተኩራለን፡፡ 3. ካልተስማማን መሪውን እንዲያሸማግለን እንጠይቃለን)

ውሳኔዎችን እንዴት እንደምናሳልፍ

(ለምሳሌ፡ እንደ አዲስ መሳሪያ መግዛት ለመሳሰሉ ትላልቅ ውሳኔዎች በጋራ እንወያይ እና መሪው የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ለእለት ከእለት የስራ ውሳኔዎች ለስራው ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ይወስናል)፡፡

 

አንዳችን ለሌላኛችን ቁርጠኛ መሆን

እንዲህ እናደርጋለን… (ለምሳሌ፡ ሳንጠየቅ እርስ በርስ እንረዳዳለን፡፡ ስኬታችንን በጋራ እናከብራለን፡፡)

 

ቀላል የአፈጻጸም ማረጋገጫ ዝርዝር

ዓላማ: ይህ መሳሪያ ከቡድን አባላትዎ ጋር ስለ አፈጻጸማቸው በተመለከተ የተደራጁና አዎንታዊ ውይይቶች እንዲያካሂዱ ይረዳዎታል፡፡ መሳሪያው ግብረ መልስን ፍትሀዊ፣ ወጥና በእድገት ላይ ያተኮረ ያደርጋል፡፡

እንዴት እንደሚጠቀሙበት: በወር አንድ ጊዜ ይህን የማረጋገጫ ዝርዝር ከእያንዳንዱ የቡድን አባል ጋር ለሚያደርጉት ውይይት በመመሪያነት ይጠቀሙበት፡፡ ውይይቱ ስለ ትችት ሳይሆን ስለ እድገት ነው፡፡ ማረጋገጫ ዝርዝሩ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡

ምሳሌ

የማረጋገጫ ዝርዝሮች

መልሶች

መፍትሄዎች

በስራ ድርሻዎ ላይ ምን በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ነው?

 

 

ምን ችግሮች እያጋጠሙዎ ነው?

 

 

ከእኔ ምን ድጋፍ ይፈልጋሉ?

 

 

የቀጣዩ ወር ግቦች ምንድን ናቸው?

 

 

Scroll to Top