የአዲስ አበባ ነዋሪ ሥራ ፈጣሪ የሆነው የ26 ዓመቱ አሊ ሁልጊዜም የአካባቢና ማህበራዊ ችግሮችን የመፍታት ፍላጎት አለወር፡፡ ከወራት ሙከራና ማጥራት በኋላ ከግብርና ተረፈ ምርት የሚሰሩ የባዮፊዩል ከሰሎችን የሚጠቀም ንጹህ የምግብ ማብሰያ ምርት ያዘጋጃል፡፡ ምርቱ በዋጋ ተመጣጣኝ፣ የጭስ ልቀቶችን በ80% የሚቀንስ እና ከኢትዮጵያ ባህላዊ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎች ጋር የሚስማማ ነው፡፡ ሆኖም አሊ ጥሩ ምርት ማዘጋጀት ብቻ በቂ እንዳልሆነ እና ስኬቱን ለማረጋገጥ ጠንካራ ወደ ገበያ ስትራቴጂ ማለፊያ ማዘጋጀት እንዳለበት ያውቃል፡፡
ለመጀመር አሊ የትኩረት ደንበኛን መለያ ቴምፕሌቱን በመጠቀም የትኩረት ደንበኞቹን ይለያል፡፡ ገበያውን በየከተማ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች፣ የገጠር አባወራዎች እና በሴት እማወራ የሚመሩ ቤተሰቦች በመመደብ እንደ ከፍተኛ የማገዶ ወጪዎች እና በቤት ውስጥ አየር መበከል ምክንያት የሚፈጠሩ የጤና ስጋቶች የመሳሰሉ ችግሮቻቸውን ለመረዳት ይሞክራል፡፡ ለከተማ ደንበኞች በዋጋ ተመጣጣኝነትና ምቹነት ላይ ያተኮረ ሲሆን ለገጠር አባወራዎች በተደራሽነት እና ለባህል አግባብነት ላይ አተኩሯል፡፡
አሊ ቀጥሎም ድጎማዎችን እና በጊዜ የተከፋፈሉ የክፍያ ዕቅዶችን የሚያካትት የዋጋ ትመና ሞዴል በማዘጋጀት የዋጋ ተመጣጣኝነት ችግርን ይፈታል፡፡ ከአካባቢ የማይክሮፋይናንስ ተቋም ጋር ትብብር በመፍጠር በየወሩ አነስተኛ ክፍያዎችን የሚከፍሉበት አማራጭ ማቅረቡ ምርቱን አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦችም ጭምር ተደራሽ ለማድረግ አስችሎታል፡፡ በስፋት የሚያከፋፍልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ አሊ የተለያዩ የከተማ ችርቻሮ ሻጮችን፣ የአካባቢ ገበያዎችን ለመምረጥና በገጠር አካባቢ ከሚሰሩ ኤንጂኦዎች ጋር ትብብር ለመመስረት የማከፋፈያ መንገድ መምረጫ ማትሪክስን ተጠቅሟል፡፡ እነዚህ የማከፋፈያ መንገዶች ወደ ከተማና የገጠር ደንበኞች ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲደርስ አስችሎታል፡፡
ለባህል አግባብነት ሌላኛው የአሊ ዋነኛ ትኩረት ነበር፡፡ ለባህል አግባብነት ማረጋገጫ ዝርዝርን በመጠቀም ምርቱን ለባህላዊ የምግብ ማብሰያ ልማዶች በሚስማማ መልኩ በማዘጋጀት ከእንጀራ መጋገሪያ ምድጃዎች እና ሌሎች የአካባቢ የምግብ ማዘጋጃዎች ጋር ያለ ምንም እንከን እንደሚሰራ ያረጋግጣል፡፡ አሊ በተጨማሪም እንደ ጭስን መቀነስና ጊዜ ቆጣቢነት ያሉ የምርቱን ጥቅሞች ለማሳየት በከተማ መንደሮችና የገጠር ማህበረሰቦች ውስጥ ገለጻዎችን አካሂዷል፡፡
የአሊ የገበያ መልዕክት ግልጽና ሳቢ ነበር፡፡ ለከተማ ነዋሪዎች የወጪ ቁጠባዎችን እና የጤና ጥቅሞችን ያብራራ ሲሆን ለገጠር አባወራዎች የደን መጨፍጨፍን መቀነስና ለአጠቃቀም ቀላል መሆን ላይ አጽንኦት አድርጓል፡፡ አሊ ወደ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ፕላትፎርሞች ዘልቆ በመግባት ምርቱን ቀደም ብለው የተቀበሉ ደንበኞች ምስክርነት የሚሰጡባቸው ትኩረት የተደረገባቸው ማስታወቂያዎችን ያካሄደ ሲሆን ይህም እምነትና ተአማኒነትን እንዲያጎለብት አስችሎታል፡፡ በተጨማሪም ምርቱን ለማስተዋወቅ፣ ተደራሽነቱን በተጨማሪ ለማጉላት ከአካባቢ ተጽእኖ ፈጣሪዎችና የማህበረሰብ መሪዎች ጋር ትብብር ፈጥሯል፡፡
ግብረ መልስ መሰብሰብ ለአሊ ወደ ገበያ የማለፍ አቀራረብ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል፡፡ አሊ የግብረ መልስ መሰብሰቢያ ቴምፕሌቱን በመጠቀም ምርቱን ለማጥራትና ጥቃቅን የአጠቃቀም ችግሮችን ለመፍታት ምርቱን ቀደም ብለው ከተቀበሉ ደንበኞች አስተያየቶችን ሰብስቧል፡፡ ይህ ተደጋጋሚ ሂደት ምርቱ የደንበኛ የሚጠበቁ ሁኔታዎችን እና የተሻሻሉ የተቀባይነት ደረጃዎችን እንደሚያሟላ አረጋግጦለታል፡፡
አሊ ስራውን በጀመረ በስድስት ወራት ውስጥ ከ1,000 በላይ ንጹህ የማብሰያ ምርቶቹን በስኬት ሸጧል፡፡ እንደ የንግድ ስራ ሞዴል ረቂቅ፣ የዋጋ ተመጣጣኝነት ስትራቴጂዎች እና የባህል አግባብነት የመሳሰሉ መሳሪያዎችን በስልት መጠቀሙ ምርቱን የትኩረት ደንበኞቹን ልዩ ፍላጎቶች ከመፍታት በተጨማሪ እንደ ዘላቂነትና የጤና መሻሻል ለማሰሉ ሰፊ ግቦች አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አስችሎታል፡፡ የአሊ ታሪክ በአግባቡ የሚተገበር የገበያ ስትራቴጂ ደንበኛን ማእከል ካደረገ ትኩረት፣ ውጤታማ ስልቶችና ሊለካ የሚችል ውጤት ጋር በጥምረት ሲተገበር ወደ ስኬት እንደሚወስድ ማረጋገጫ ነው፡፡