ዮናስ ላለፉት ሶስት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በአነስተኛ የንጹህ ማብሰያ ምድጃ የንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቷል፡፡ ስራውን የጀመረው የተሻሻሉ የባዮማስ ምድጃዎችን በማምረት፣ ምርቶቹን በአብዛኛው ለከተማ አባወራዎች እና በከተማ ዙሪያ ለሚገኙ አነስተኛ የምግብ አቅራቢዎች በመሸጥ ነው፡፡ ስራውን ሲጀምር የሽያጭ ሂደቱ ቋሚ የነበረ ቢሆንም ከሁለት አመት በኋላ ግን የሽያጭ እድገቱ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ ዮናስ በዘላቂነት ስራውን ማሳደግ የሚፈልግ ከሆነ የምርቱን አቅርቦት አሁን ካሉት ደንበኞችም ባሻገር ማስፋት እንዳለበት ተገነዘበ፡፡
ዮናስ የተማረውን ትምህርት በመተግበር ጀመረ – ወቅታዊ ገበያዎን መረዳት፡፡ የደንበኛ መረጃ ወርክሺትን በመጠቀም ወቅታዊ ተጠቃሚዎቹ እነ ማን እንደሆኑ ለይቶ ያውቃል – እነዚህ በዋበነኝነት በከተማ መንደሮች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ በየዕለቱ ምግብ የሚያበስሉና ለማገዶ ቆጣቢነት ቅድሚያ የሚሰጡ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች እንደሆኑ ያውቃል፡፡ ዮናስ በተጨማሪም አብዛኞቹ ደንበኞቹ ስለ ምርቱ ሲነገር ሰምተው ወይም ወደ ቤተ ሙከራው በቀጥታ ለመግዛት እንደሚመጡ ለማየት የገበያ ተደራሽነት ካርታን ይጠቀማል፡፡ ይህም የት በጥሩ ሁኔታ እንደደረሰና የት እንዳልደረሰ ለመረዳት ይረዳዋል፡፡
ቀጥሎም ዮናስ ወደ ትምህርት 2 – አዲስ የደንበኛ ምድቦችን መለየት ያልፋል፡፡ በአካባቢ ኤንጂኦ አጋር እርዳታ እንደ የገጠር አባወራዎች፣ በሴቶች የሚመሩ የህብረት ሥራ ማህበራት እና የትምህርት ቤት ማድ ቤቶች የመሳሰሉ አዲስ የደንበኛ ቡድኖችን ያጠናል፡፡ ከዚያም የአዲስ የደንንበኛ ምድብ መፈለጊያን ይሞላ እና የገጠር ማህበረሰቦች ብዙ ጊዜያቸውን የማገዶ እንጨት ለመሰብሰብ እንደሚያባክኑ እና በቤት ውስጥ ጭስ ምክንያት ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ያውቃል፡፡ የደንበኛ ምድብ መገምገሚያ ማረጋገጫ ዝርዝርን በመጠቀም ምድጃዎቹን ከሀዋሳ ውጭ በቅርበት በሚገኙ መንደሮች መሸጥን ለመሞከር ይወስናል፡፡
ዮናስ ወደ ማከፋፈል ከመግባቱ በፊት ተፎካካሪውን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ይፈልጋል፡፡ በትምህርት 3- የተፎካካሪ ትንተና ማካሄድ ስር የተፎካካሪ መለያ ዝርዝርዝርን በመጠቀም በአካባቢ ሱቆች ውስጥና በኦንላይን የሚገኙ ሌሎች የምድጃ አይነቶችን ይዘረዝራል፡፡ ከዚያም የተፎካካሪ ማነጻጸሪያ ማትሪክስን በመጠቀም የምርቶቹን ባህሪያትና ዋጋዎች ያነጻጽር እና ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ምርቶች ርካሽ ቢሆኑም ከሱ ምርት ጋር ተመሳሳይ የረጅም ጊዜ አገልግሎት እንደማያቀርቡ ወይም ግለትን እንደማይቋቋሙ ያውቃል፡፡ ይህን ግንዛቤ የልዩ ጥቅም ዕቅድ ወርክሺትን በመጠቀም ስለ ምርቱ ጥቅም የተመለከተ ጠንካራ መልዕክት ለማዘጋጀት ይጠቀምበታል፡፡
ዮናስ ይህን እውቀት በመታጠቅ በትምህርት 4 – ትክክለኛ የማከፋፈያ መንገዶችን መምረጥ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የማከፋፈያ መንገድ መስማማት ማረጋገጫውን በመጠቀም የማከፋፈያ መንገዱ ከገጠር የደንበኛ ልማዶች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ ከአካባቢ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር እንደ ወኪል ሆነው እንዲሰሩለት በትብብር መስራት ይጀምራል፡፡ ቀላል የሙከራ የማከፋፈያ መንገድ የድርጊት ዕቅድ ያዘጋጅ እና ለሁለት ሴቶች ስለ ምድጃዎቹ ገለጻ እንዲያደርጉና ቤተ ለቤት እንዲሸጡ ስልጠና ይሰጣል፡፡ የአጋር ዝግጁነት ማረጋገጫ ዝርዝርን አጋሮቹ ስለ ምርቱ መረዳታቸውን እና ከሽያጭ በኋላ ድጋፍ ማቅረብ ስለመቻላቸው ለማረጋገጥ ይጠቀምበታል፡፡
ምድጃዎቹን በአዳዲስ ቦታዎች ለማስተዋወቅ ዮናስ ወደ ትምህርት 5- የማስተዋወቂያ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ግብይት ያልፋል፡፡ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ፕላትፎርም ማዘጋጃ ማረጋገጫ ዝርዝርን በመጠቀም መሰረታዊ የፌስ ቡክ ገጽ እና የቴሌግራም አካውንት ይከፍታል፡፡ ቀላል የቪዲዮ ጽሁፍ ቴምፕሌትን በመጠቀም እውነተኛ ተጠቃሚዎች ምድጃውን በመጠቀም ምግብ ሲያበስሉ የሚያሳዩ አጭር ቪዲዮዎች ይቀርጻል፡፡ ይህን የይዘት ካላንደር ቴምፕሌትን በመጠቀም በየ ሳምንቱ ከመለጠፍ በተጨማሪ በምርቱ እርካታ ያገኙ ደንበኞችን ስለ ተሞክሮዎቻቸው እንዲያጋሩ ይጠይቃል፡፡ በሳምንታት ውስጥ በከተማው ውስጥ ካሉ ሰዎች ተጨማሪ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ያያል፡፡
በመጨረሻም ዮናስ ትምህርት 6- የደንበኛ ግብረ መልስን መከታተልን በመከተል ግብረ መልስ በመደበኛነት የሚሰበስብ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በአቅርቦትና የክትትል ጉብኝቶች ወቅት ቀላል የግብረ መልስ ቅጽ ይጠቀማል፡፡ የግብረ መልስ ማጠቃለያ መዝገብን በመጠቀም መደበኛ ቅሬታዎችና ጥቆማዎችን ይከታተላል፡፡ አንደኛው በተደጋጋሚ የሚሰጠው አስተያየት ምድጃው ለአረጋውያውን ሰዎች በጣም ትልቅ ነው የሚል ሲሆን ዮናስ ቀለል ያለ ዲዛይን ለማዘጋጀት ከቡድኑ ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ የበፊትና በኋላ መከታተያን በመጠቀም ይህ ለውጥ ያመጣውን ውጤት ይከታተል እና የደንበኛ እርካታ በከፍተኛ ደረጃ እንደጨመረ ያረጋግጣል፡፡
በአሁኑ ወቅት የዮናስ የንግድ ሥራ የከተማ ቤተሶች ጋር ብቻም ሳይሆን የገጠር አባወራዎችና አነስተኛ ተቋማት ጋርም ይደርሳል፡፡ ዮናስ ከደንበኞቹ ጋር ግንኙነት ማድረጉን ለመቀጠል፣ ምርቱን ለማሻሻል እና ለተጨማሪ እድገት ለማቀድ የተማራቸውን መሳሪያዎች መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡