Skip to content
ለንጹህ ማብሰያ ስራ ፈጣሪዎች እንደ መመሪያ እንዲያገለግል በፊደል ቅደም ተከተል የተዘጋጀ ማመሳከሪያ
- ተፎካካሪ – ተመሳሳይ ምርት ወይም አገልግሎት የሚያቀርብ ሌላ የንግድ ድርጅት ነው፡፡
- የደንበኛ ምድብ – የሚያገለግሏቸው ወይም ሊያገለግሏቸው የሚፈልጓቸው ልዩ የተጠቃሚዎች ቡድን ነው (ለምሳሌ፡ የከተማ ቤተሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች)፡፡
- የደንበኛ ግብረ መልስ – ከተጠቃሚዎች በምርትዎ ላይ ስላላቸው ተሞክሮ በተመለከተ መረጃ መሰብሰብ ነው፡፡
- የማከፋፈያ መንገድ – ምርትዎ ደንበኞች ጋር የሚደርስበት መንገድ ነው (ለምሳሌ፡ የአካባቢ ወኪል፣ ኤንጂኦ፣ የችርቻሮ ሱቅ)፡፡
- የገበያ ማስፋፊያ – ወደ አዳዲስ ደንበኞች ጋር በመድረስ ወይም ወደ አዳዲስ ቦታዎች በመግባት የንግድ ሥራዎን ማሳደግ ነው፡፡
- የገበያ ተደራሽነት ካርታ – ደንበኞችዎ በአሁኑ ወቅት ምርትዎን እንዴት እንደሚያገኙ የሚያሳይ የእይታ መሳሪያ ነው፡፡
- የመጀመሪያ ሙከራ – ከሙሉ ፕሮግራም ወይም ስትራቴጂ ትግበራ በፊት የሚካሄድ አነስተኛ ደረጃ ሙከራ ነው፡፡
- የደንበኛ ምድብ መገምገሚያ ማረጋገጫ ዝርዝር – እጅግ ተስፋ ሰጪ አዲስ የደንበኛ ቡድን ለመምረጥ የሚረዳዎ መሳሪያ ነው፡፡
- የማህበራዊ ትስስር ገጽ ግብይት – ምርትዎን ለማስተዋወቅና ከተጠቃሚዎች ጋር ለመገናኘት እንደ ፌስቡክ ወይም ዋትስአፕ የመሳሰሉ ፕላትፎርሞችን መጠቀም፡፡
- የልዩ ጥቅም ዕቅድ – ደንበኞች ለምን ከሌሎች ምርቶች ይልቅ የእርስዎን ምርት መምረት እንዳለባቸው የሚናገር ግልጽ መግለጫ ነው፡፡