በኢትዮጵያ ንጹህ የማብሰያ የንግድ ሥራ ዘርፍ የገበያ ማስፋፊያ

ትምህርት 1: ወቅታዊ ገበያዎን መረዳት

 

ፍቺ/ትርጉም

ወቅታዊ ገበያዎን መረዳት ማለት ነባር ደንበኞችዎ እነ ማን እንደሆኑ፣ ምርትዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ፣ ምርቱን ከየት እንደሚገዙ እና የእርስዎን የምርት ምልክት ለምን ከሌሎች እንደመረጡ ማወቅ ነው፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች:

  • ወቅታዊ ደንበኞችዎ እነ ማን እንደሆኑ መለየት፡፡
  • የማብሰያ ምድጃዎን ወይም ንጹህ የማብሰያ ምርትዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ መረዳት፡፡
  • ምን እንደሚወዱና ምን ሊሻሻል እንደሚችል ማወቅ፡፡

 

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • ለፍተኛ የደንበኛ አይነቶችዎ ዝርዝር ያዘጋጁ (ለምሳሌ፡ የከተማ ቤተሰቦች፣ አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች)፡፡
  • የሚከተሉትን አይነት ጥያቄዎች ይጠይቁ: ይህን ምድጃ የሚጠቀሙት ለምንድን ነው? በየ ምን ያክል ጊዜ? ስለ ምድጃው ምን ያስባሉ?
  • እንደ የደንበኛ ግብረ መልስ መስጫ ቅጾች ወይም ኢ-መደበኛ ቃለ መጠይቆች ያሉ ቀላል መሳሪያዎችን ይጠቀሙ፡፡
  • ደንበኞችዎ በአሁኑ ወቅት ምርትዎን እንዴት እንደሚያገኙ በካርታ ያሳዩ፡፡

 

ትምህርት 2: አዲስ የደንበኛ ምድቦችን መለየት

 

ፍቺ/ትርጉም:

አዲስ የደንበኛ ምድቦችን መለየት ማለት በቦታ፣ የገቢ ደረጃ፣ የማገዶ ምርጫ ወይም የአጠቃቀም ልማዶች ላይ ተመስርቶ ያልተደረሱ የተጠቃሚ ቡድኖችን ማወቅ ነው፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች:

  • ከአሁኑ ገበያዎ ባሻገር ያሉ የተለያዩ የዕጩ ተጠቃሚዎች አይነቶችን ማጥናት፡፡
  • ኢላማ የሚያደርጓቸውን እጅግ ተስፋ ሰጪ የደንበኛ ቡድኖች መምረጥ፡፡
  • መልዕክትዎን ወይም አቅርቦትዎን ለእነሱ ፍላጎቶች እንዲስማማ አድርጎ ማስማማት፡፡

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • ስለ የገጠር ማህበረሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ማእከላት፣ የጎዳና ላይ የምግብ አቅራቢዎች፣ በሴቶች የሚመሩ የህብረት ሥራ ማህበራት ወይም ተቋማት ያስቡ፡፡
  • የትኞቹ ቡድኖች በቤት ውስጥ የአየር መበከል እጅግ እንደሚጠቁ ወይም አብዛኛውን ወጪያቸውን ለማገዶ እንደሚያውሉ ያጥኑ፡፡
  • የደንበኛ ምድብ በሚመርጡበት ወቅት የገቢ ደረጃዎችን፣ የምግብ አበሳሰል ልማዶችን እና የማገዶ መገኘትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ፡፡
  • ሙሉ ማስፋፊያ ከመተግበርዎ በፊት አነስተኛ የመጀመሪያ ሙከራዎች ለማድረግ ይሞክሩ፡፡

 

ትምህርት 3: የተፎካካሪ ትንተና ማካሄድ

 

ፍቺ/ትርጉም:

የተፎካካሪ ትንተና ማካሄድ ማለት ሌሎች ተመሳሳይ ምርቶችን የሚያቀርቡ የንግድ ድርጅቶችን መለየት እና እራስዎን በተሻለ አቋም ላይ ለማስቀመጥ ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸውን መረዳት ነው፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች:

  • ዋና ዋና ተፎካካሪዎችዎ እነጀ ማን እንደሆኑ መዘርዘር፡፡
  • ምን እንደሚያቀርቡና ዋጋቸው ስንት እንደሆነ መረዳት፡፡
  • የእርዎን የንግድ ሥራ ልዩ ማድረግና የተሻለ ጥቅም ለማቅረብ የሚያስችሉ መንገዶችን መፈለግ፡፡

 

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • ተመሳሳይ ምርቶችን ለማግኘት የአካባቢ ሱቆችን ይጎብኙ፣ ደንበኞችን ያናግሩ ወይም ከኢንተርኔት ላይ ይፈልጉ፡፡
  • የምርት ባህሪያትን፣ ዋጋን፣ ስርጭትን እና የገበያ ስትራቴጂዎችን ያነጻጽሩ፡፡
  • ክፍተቶችን ይመልከቱ — ደንበኞች ያልረኩት በምን ላይ ነው?
  • እንዴት ማሻሻል ወይም ለየት ያለ ነገር (ለምሳሌ፡ የተሻለ አገልግሎት፣ ዲዛይን ወይም የክፍያ አማራጮች) ማቅረብ እንደሚችሉ ይወስኑ፡፡

 

ትምህርት 4: ትክክለኛ የማከፋፈያ መንገዶችን መምረጥ

 

ፍቺ/ትርጉም:

ትክክለኛ የማከፋፈያ መንገዶችን መምረጥ ማለት ምርትዎን ለትኩረት ደንበኞችዎ ውጤታማ በሆነ መንገድና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርቡባቸውን ምርጥ ዘዴዎች መምረጥ ነው፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች:

  • ምርትዎን የሚያከፋፍሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች ማወቅ፡፡
  • በደንበኛ ምድብዎ ላይ ተመስርተው እጅግ ተስማሚ መንገዶችን መምረጥ፡፡
  • ለረጅም ጊዜ ትብብር ድጋፍ የሚያደርጉ ትብብሮችን መመስረት፡፡

 

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • አማራጮች ቀጥተኛ ሽያጮችን፣ የችርቻሮ መደብሮችን፣ ኤንጂኦዎችን፣ ተንቀሳቃሽ አቅርቦትን ወይም ከአካባቢ ወኪሎች ጋር አብሮ መስራትን ያጠቃልላሉ፡፡
  • የማከፋፈያ መንገዱን የትኩረት ደንበኞችዎ ከሚገዙበት መንገድ ጋር ያስማሙ – ለምሳሌ፡ የገጠር ደንበኞች የአካባቢ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ወይም የመንደር ውስጥ ሱቆችን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡
  • በመጀመሪያ አንድ የማከፋፈያ መንገድ ይሞክሩና ከዚያም አንዴ ይህ መሳካቱን ካዩ በኋላ ያስፋፉ፡፡
  • ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎትን እና ከሽያጭ በኋላ ድጋፍን ለማረጋገጥ አከፋፋዮችን በጥሩ ሁኔታ ያሰልጥኑ፡፡

 

ትምህርት 5: የማስተዋወቂያ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ግብይት

 

ፍቺ/ትርጉም:

የማህበራዊ ትስስር ገጽ ግብይት ማለት ታሪኮችን ለማጋራት፣ የምርትዎን ጥቅሞች ለማሳየት እና ከእጩ ደንበኞች ጋር ለመገናኘት እንደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዋትስ አፕ ወይም ዩቲዩብ ያሉ መድረኮችን መጠቀም ነው፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች:

  • ለንግድ ሥራዎ መሰረታዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃዎች ማዘጋጀት፡፡
  • ታሪክዎን የሚናገር እና ምርትዎ በተግባር ጥቅም ላይ ሲውል የሚያሳይ ይዘት ማዘጋጀት፡፡
  • ደንበኞችን ማሳተፍ እና ምን እንደሚሰራ ማየት፡፡

 

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • ብዙ ኢትዮጵያውያን በየዕለቱ በሚጠቀሟቸው እንደ ፌስቡክ ወይም ዋትስ አፕ በመሳሰሉ ነጻ ፕላትፎርሞች ይጀምሩ፡፡
  • ምድጃዎ እንዴት እንደሚሰራ ወይም በምርትዎ ደስተኛ የሆኑ ተጠቃሚዎች ምስክርነትን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ያጋሩ፡፡
  • በመደበኛነት ይለጥፉ እንዲሁም ለአስተያየቶች ወይም መልዕክቶች ምላሽ ይስጡ፡፡
  • ለደንበኞችዎ በቀጥታ የሚናገሩ የአካባቢ ቋንቋዎችን እና የእይታ መርጃዎችን ይጠቀሙ፡፡
  • ተሳትፎን እየተከታተሉ ምን ከፍተኛ ትኩረት እንዳገኘ መሰረት በማድረግ ስትራቴጂዎን ያስተካክሉ፡፡

 

ትምህርት 6: የደንበኛ ግብረ መልስን መከታተል

 

ፍቺ/ትርጉም:

የደንበኛ ግብረ መልስን መከታተል ማለት ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻያ ለማድረግ እንዲረዳዎ ከተጠቃሚዎች በምርትዎ ላይ ስላላቸው ተሞክሮ የተመለከተ መረጃ መሰብሰብና መተንተን ነው፡፡

 

የትምህርቱ ዓላማዎች:

  • ከተጠቃሚዎች እንዴት ግብረ መልስ እንደሚሰበሰብ ማወቅ፡፡
  • የደንበኞች አስተያየቶችን ማደራጀት እና መተንተን፡፡
  • ምርትዎን፣ አገልግሎትዎን ወይም የግብይት ዘዴዎን ለማሻሻል አስተያየቶችን መጠቀም፡፡

 

ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:

  • በአቅርቦት፣ የክትትል ጉብኝቶች ወይም የዋትስ አፕ የዳሰሳ ጥናቶች ወቅት ጥያቄዎችን መጠየቅ፡፡
  • ለተለመዱ ቅሬታዎች ወይም አስተያየቶች መዝገብ ማዘጋጀት፡፡
  • በግብረ መልስ ላይ ተመስርቶ አነስተኛ ለውጦች ማድረግና ለውጡ መስራቱን መፈተሽ፡፡

በማሻሻያዎች መደሰትና አዎንታዊ ውጤቶችን ለቡድንዎና አጋሮችዎ ማጋራት፡፡

Scroll to Top