ወቅታዊ ደንበኞችዎ እነ ማን እንደሆኑ በግልጽ ለመለየት ይረዳዎታል፡፡
የደንበኛ አይነት:
(ለምሳሌ፡ የከተማ ቤተሰቦች፣ የጎዳና ላይ የምግብ አቅራቢዎች፣ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች)
|
ጥያቄ |
የእርስዎ መልስ |
|
የሚገኙት የት ነው? (ከተማ፣ አነስተኛ ከተማ፣ መንደር ውስጥ) |
|
|
የገቢ ደረጃቸው ምን ያክል ነው? (አነስተኛ፣ መካከለኛ፣ ከፍተኛ) |
|
|
በአሁኑ ወቅት የሚጠቀሙት ማገዶ ምንድን ነው? (እንጨት፣ ከሰል፣ ኤልፒጂ፣ ወዘተ) |
|
|
የቤተሰቡ አባላት ወይም የንግድ ድርጅቱ ሰራተኞች ብዛት ስንት ነው? |
|
|
የእርስዎን ምርት ከሌሎች ምርቶች የሚመርጡት ለምንድን ነው? |
|
|
የማብሰያ ምድጃዎን በየ ምን ያክል ጊዜ ይጠቀማሉ? በየቀኑ/ በየ ሳምንቱ/ አልፎ አልፎ |
ቀላል የደንበኛ ግብረ መልስ መስጫ ቅጽ
ይህን ቅጽ ከተጠቃሚዎችዎ በቀጥታ አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ይጠቀሙት፡፡
ፈጣን የግብረ መልስ ጥያቄዎች:
- ይህን ምድጃ ለምን ያክል ጊዜ ተጠቅመውታል?
☐ ከ1 ወር ያነሰ ☐ ከ1–3 ወራት ☐ ከ3–6 ወራት ☐ ከ6 ወራት በላይ - ከምድጃው እጅግ የወደዱት ነገር ምንድን ነው?
(ለምሳሌ፡ ማገዶ ይቆጥባል፣ የሚያወጣው አነስተኛ ጭስ ነው፣ ለአጠቃቀም ቀላል ነው) - ከምድጃው የሚቸገሩበት ወይም የሚያናድድዎ ነገር አለ?
☐ አዎ ☐ አይ
- ይህን ምድጃ ሌሎች እንዲጠቀሙት ይመክራሉ?
☐ አዎ ☐ አይ ☐ ምናልባት - ይህን ምድጃ ለእርስዎ የተሻለ የሚያደርጉት ምን ለውጦች ቢደረጉ ነው?
☐የዋጋ ☐የጥራት ☐የመጠን ☐የረጅም ጊዜ አገልግሎት ☐የማገዶ ፍጆታ ☐የአጠቃቀም ወይም አገልግሎት
የገበያ ተደራሽነት ካርታ
ደንበኞችዎ በአሁኑ ወቅት ምርትዎን እንዴት እንደሚያገኙ ለይቶ ያሳውቃል
ደረጃ በደረጃ መመሪያዎች:
- ደንበኞች ምርትዎን የሚያገኙባቸውን የተለያዩ መንገዶች ይምረጡ፣ ለምሳሌ:
☐ በሱቅዎ ውስጥ የሚካሄድ ቀጥተኛ ሽያጭ ☐ በወኪል ወይም አከፋፋይ በኩል መግዛት ☐ በኤንጂኦ ወይም የመንግስት ፕሮግራም በኩል ማግኘት ☐ ከኢንተርኔት ላይ ማየት ወይም እርስዎን ማናገር
- ከእያንዳንዱ አውድ አጠገብ ማስታወሻዎች ይጻፉ፣ ለምሳሌ:
- ደንበኞች ምን ያክል ርቀት እንደሚጓዙ
- ምን ያክል ጊዜ ወይም ገንዘብ እንደሚወስድ
ከገዙ በኋላ ድጋፍ የሚያገኙ ስለመሆን አለመሆኑ