ለጀማሪ የቢዝነስ መስራቾች ስልጠና

የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነችው የ23 ዓመቷ የቲኢቪኢቲ ተመራቂዋ ህይወት ሁልጊዜም በማህበረሰቧ ውስጥ ለውጥ የማምጣት ህልም አላት፡፡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ በቤተሰብ የማብሰያ ምርቶች ላይ አተኩሮ የሚሰራ የአካባቢ የንጹህ ኢነርጂ ኢኒሺየቲቭ ትቀላቀላለች፡፡ ብዙ ቤተሰቦች አሁንም ከፍተኛ ሀይል በሚጠቀሙ እና የተግባር ችግሮች ባሉባቸው ባህላዊ ምድጃዎች ላይ ጥገኛ እንደሆኑ ትገነዘባለች፡፡ ሂወት የራሷን በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ውጤታማ የባዮማስ የማብሰያ ምድጃዎች የምታመርትበትና የምታከፋፍልበት የንግድ ስራ ለመጀመር ትወስናለች፡፡

 

መጀመሪያ ላይ ጉዞው ግራ አጋቢ ነበር፡፡ በውሱን ገንዘብ እና ምንም መደበኛ የንግድ ስራ ስልጠና ሳይኖራት ህይወት ጊዜዋን ለመጠቀም፣ ግልጽ ግቦችን ለመወሰን፣ እና ከአቅራቢዎችና ደንበኞች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ተቸግራ ነበር፡፡ ነገር ግን ከመተው ይልቅ በኢትዮጵያ የንጹህ ኢነርጂ ዘርፍ ውስጥ ከወጣት መስራቾች ጋር በሚስማማ የስራ ፈጠራ ዝግጅት ፕሮግራም ውስጥ ትመዘገባለች፡፡ በዚህ ፕሮግራም አማካኝነት ህይወት ወደጀማሪነት ጉዞዋ ያሸጋገሯትን ወሳኝ ክህሎቶች ትማራለች፡፡

 

ህይወት እንደ በስድስት ወራት ውስጥ 200 ምድጃዎች አምርቶ መሸጥ የመሳሰሉ የSMART ግቦችን በመወሰን ትጀምራለች፡፡ ይህ ግልጽ ፍኖተ ካርታ የሰጣት ከመሆኑም በተጨማሪ ትልቁን ህልሟን ትርጉም ወዳላቸው ደረጃዎች እንድትከፋፍል ረድቷታል፡፡ እንደ ሳምንታዊ የዕቅድ ማዘጋጃዎችና የቅደም ተከተል መስጫ ያሉ የጊዜ አጠቃቀም መሳሪያዎችን በመጠቀም እንደ የምርት ዲዛይን ማሻሻያዎች እና የደንበኛ ተደራሽነት ባሉ ከፍተኛ ውጤት በሚያስገኙ ስራዎች ላይ በማተኮር የምርት ስራዎችን ስልጠና ላላቸው የቀጠረቻቸው ባለሙያዎች ትመድባለች፡፡

 

መንገዱ እንቅፋት ያልነበረበት አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ላይ ዋና ዋና አቅራቢዎች ቁሳቁሶችን በወቅቱ አላቀረቡላትም፣ የመጀመሪያ ትእዛዟን አዘግይተውባታል፡፡ ህይወት ከመሸበር ይልቅ ስለ ዝግጁነት እና የእድገት አስተሳሰብ የተማረችውን ትምህርት ትተገብራለች፡፡ ሁኔታውን እንደ መማሪያ እድል ያየችው ህይወት የወደፊት መዘግየቶችን ለማስቀረት አማራጭ አቅራቢዎችን በመፈለግ የንብረት መከታተያ ስርዓቷን ታሻሽላለች፡፡

 

ሂወት ከባለሀብቶችና አጋሮች ጋር ግኝኑነት ባደረገችበት ወቅት ስለ ንጹህ ማብሰያዋ ውጤት – ምድጃዎቿ እንዴት ጭስ እንደሚቀንሱ፣ የሴቶችን ጊዜ እንደሚቆጥቡ እና የማገዶ ወጪዎችን እንደሚቆጥቡ ጠንካራ ታሪኮችን ለመንገር የውጤታማ ግንኙነት ስልቶችን ተጠቅማለች፡፡ ሳቢ የታሪክ አነጋገሯ የአካባቢ ኤንጂኦ ትኩረት በመሳብ ምክር እንድታገኝ ከማስቻሉም በተጨማሪ ምርቷን እንድታስፋፋ ድጋፍ ሊያደርጉላት ፍላጎት ካላቸው የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር አስተዋውቋታል፡፡

 

ሂወት ወጥነት ያለው ትስስር በመፍጠር ጠንካራ የድጋፍ ስርዓት ገንብታለች፡፡ በንጹህ ኢነርጂ አውደ ርዕዮች ላይ ተሳትፋለች፣ የአፍሪካ ስራፈጣሪዎች የኦንላይን መድረኮችን ተቀላቅላለች እንዲሁም በዘርፉ ውስጥ በሴት ከሚመሩ ጀማሪዎች ጋር ግንኙነት ፈጥራለች፡፡ እነዚህ ግንኙነቶችም ምክር መስጠት ብቻም ሳይሆን በገጠር አካባቢዎች የሽያጭ ወኪል ከሆኗት የሴቶች የህብረት ስራ ማህበራት ጋር ትብብር እንድትፈጥር አስችለዋታል፡፡

 

ቡድኑ እያደገ ሲመጣ ህይወት ለሰራተኞቿ ውጤታማ በሆነ መልኩ ስራ መመደብ እና አቅማቸውን ማጎልበት እንዳለባት ትማራለች፡፡ በጠንካራ ጎኖች ላይ ተመስርታ የስራ ድርሻዎችን መድባለች፣ መደበኛ የግብረ መልስ ማግኛ ክፍለ ጊዜዎችን አካሂዳለች እንዲሁም በትናንሽ ድሎች በመደሰት ሞራልና ምርታማነትን አጠናክራለች፡፡ በማርኬቲንግ እና የኦፕሬሽኖች ቡድኖቿ መካከል የአቅርቦት የጊዜ ሰለሌዳን በተመለከተ አለመግባባት በተፈጠረበት ወቅት ውይይቶችን ለማካሄድ፣ ስረ መንስኤዎችን ለመለየት እና የተሻሉ የቅንጅት አሰራሮችን ለመተግበር የግት አፈታት ስልቶችን ተጠቅማለች፡፡

 

እንደ የእቃዎች ዋጋዎች መቀያየር እና የገበያ ፍላጎቶች መቀያየር ያሉ እርግጠኛ መሆን የማይቻልባቸው ነገሮች ሲያጋጥሟት ህይወት እንደ የSWOT ትንተናና የወጪ-ጥቅም ግምገማዎች ያሉ የውሳኔ አሰጣጥ ማዕቀፎችን ትተገብራለች፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች ውሱን ዳታ ባላት ጊዜም እንኳን በመረጃ የተደገፉ ምርጫዎችን በፍጥነት እንድትመርጥ ረድተዋታል፡፡

Scroll to Top