Skip to content
- የወጪ-ጥቅም ትንተና – ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ውሳኔ ለመስጠት ጥቅሞችና ጉዳቶችን ማነጻጸሪያ ዘዴ ነው፡፡
- መመደብ – ውጤታማነትና የቡድን ስራን ለማሻሻል ስራዎችን በክህሎቶቻቸው ላይ ተመስርቶ ለሌሎች መመደብ ነው፡፡
- ግብረ መልስ – አፈጻጸምን ለማሻሻል እንዲረዳ ከሌሎች ሰዎች የሚገኙ ገንቢ አስተያየቶች ወይም ጥቆማዎች ናቸው፡፡
- ግብ መወሰን – ለግልና የንግድ ስራ እድገትዎ በመመሪያነት የሚያገለግሉ ግልጽና የተግባር ኢላማዎችን መግለጽ ነው፡፡
- የእድገት አስተሳሰብ – ችሎታዎች በጥረት፣ ትምህርትና ጽናት ሊያድጉ ይችላሉ ብሎ ማመን ነው፡፡
- አማካሪ – በሙያዎ እንዲያድጉ ለመርዳት መመሪያና ምክር የሚሰጥዎ ልምድ ያለው ሰው ነው፡፡
- ትስስር – እውቀት፣ ድጋፍ እና እድሎችን ለመለዋወጥ ሙያዊ ግንኙነቶችን መመስረት ነው፡፡
- የችግር አፈታት – መንስኤዎችን በመተንተን እና አማራጮችን በመሞከር ለችግሮች ውጤታማ መፍትሄ መፈለግ ነው፡፡
- ዝግጁነት – እንቅፋቶችን የማለፍ እና በጫና ውስጥም ወደፊት የመቀጠል ችሎታ ነው፡፡
- የSMART ግቦች – ዓላማ ተኮር፣ ሊለኩ የሚችሉ፣ ሊሳኩ የሚችሉ፣ ተገቢና በገዜ የተገደቡ ግቦች ናቸው፡፡
- ባለድርሻ አካል – እንደ ደንበኞች፣ ባለሀብቶች ወይም አጋሮች ያሉ በእርስዎ ስራ ተጽእኖ የሚፈጠርባቸው ወይም ለንግድ ስራዎ ፍላጎት ያላቸው የትኛውም ሰዎች ናቸው፡፡
- የSWOT ትንተና – ከንግድ ስራዎ ጋር በተያያዘ ጠንካራ ጎኖችን፣ ደካማ ጎኖችን፣ እድሎችን እና ስጋቶችን የሚገመግሙበት መሳሪያ ነው፡፡
- የጊዜ ምደባ – ቀንዎን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር ለስራዎች የተወሰኑ ሰዓቶችን መመደብ ነው፡፡
- የአስቸኳይ እና አስፈላጊ ማትሪክስ – በአስቸኳይነትና አስፈላጊነታቸው ላይ ተመስርቶ የትኞቹ ስራዎች አሁን፣ ቆይቶ እንደሚሰሩ፣ እንደሚመደቡ ወይም እንደሚተዉ ለመወሰን የሚያገለግል መሳሪያ ነው፡፡
- ራዕይ – የንግድ ስራዎ ወደፊት ምን ላይ እንዲደርስ እንደሚፈልጉ የተመለከተ ግልጽ ራዕይ ነው፡፡
- ስራና ህይወትን ማመጣጠን – መሰላቸትን ለማስቀረትና ጤናማ ሆኖ ለመቀጠል በስራና የግል ህይወትዎ መካከል ያለውን ጊዜ ማመጣጠን ነው፡፡