ትምህርት 1. ግብ መወሰን እና ራዕይ ማስማማት
ፍቺ/ትርጉም:
ግብ መወሰን ለስራ ፈጣሪነት ጉዞዎ ትኩረት መስጠትዎን እና አቅጣጫ ማስያዝዎን በማረጋገጥ ከረጅም ጊዜ ዓላማዎችዎ ጋር የሚስማሙ ግልጽና የተግባር ዓላማዎችን የመወሰን ሂደት ነው፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- የዕለት ከዕለት ተግባሮችን ከረጅም ጊዜ ግቦች ጋር የማስማማት አስፈላጊነትን መረዳት፡፡
- እንዴት የSMART (ዓላማ ተኮር፣ ሊለኩ የሚችሉ፣ ሊሳኩ የሚችሉ፣ ተገቢ፣ በጊዜ የተገደቡ) ግቦች ማዘጋጀት እንደሚቻል መማር፡፡
- አካሄድን ለመከታተል እና በተነሳሽነት ለመቀጠል ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- የግልና የንግድ ስራ ራዕይዎን መግለጽ፡፡
- ረጅም ግቦችን ወደ የአጭር ጊዜ መለኪያዎች መከፋፈል፡፡
- ለማደራጀት እንደ የግብ መወሰኛ ቴምፕሌቶች ወይም የራዕይ ሰሌዳዎች የመሳሰሉ መሳሪያዎችን መጠቀም፡፡
- በግብረመልስና ውጤቶች ላይ ተመስርቶ ግቦችን መገምገምና ማስተካከል፡፡
ትምህርት 2. የጊዜ አጠቃቀምና ቅደም ተከተል መስጠት
ፍቺ/ትርጉም:
የጊዜ አጠቃቀም ከፍተኛ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ስራዎች ጊዜን ውጤታማ በሆነ መልኩ ማደራጀትና መመደብን የሚይዝ ሲሆን ቅደም ተከተል መስጠት ሀብቶች ከፍተኛ ውጤት ላላቸው ስራዎች መመደባቸውን ያረጋግጣል፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- ተወዳዳሪ ፍላጎቶችን ለማስተዳደር እንደ የጊዜ ምደባና ቅደም ተከተል መስጫ ዘዴዎች የመሳሰሉ ስልቶችን ማወቅ፡፡
- በአስቸኳይ እና አስፈላጊ ስራዎች መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ፡፡
- መረበሾችን ለመቀነስና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን መለየት፡፡
ዋና ዋና የትምህርት ነጥቦች:
- ከፍተኛ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ስራዎች ልዩ ጊዜ መመደብ፡፡
- መሰላቸትን ለማስቀረትና ስራ-ህይወትን ለማመጣጠን ገደቦች ማስቀመጥ፡፡
- ውጤታማ አለመሆኖችን ለመለየት ለስራዎች የተሰጠውን ጊዜ መከታተል፡፡
ትምህርት 3. ዝግጁነትና የአእምሮ ጥንካሬን ማጎልበት
ፍቺ/ትርጉም:
ዝግጁነት እንቅፋቶችን የመላመድና የመወጣት ችሎታ ሲሆን የአእምሮ ጥንካሬ ስራ ፈጣሪዎችን በጫና ውስጥም ትኩረት ሰጥተውና አዎንታዊ አመለካከት ይዘው እንዲቀጥሉ ያስችላቸዋል፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- ጫናን፣ ተቀባይነት ማጣትን እና ውድቀትን ማለፊያ ስትራቴጂዎችን ማጎልበት፡፡
- የስነ ልቡና ደህንነትን ለማስጠበቅ የአስተዋይነት ስልቶችን መማር፡፡
- እንደ የራስ ገለጻና የምስጋና አሰራሮች ያሉ ዝግጁነትን ማጠናከሪያ ልማዶችን ማጎልበት፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- ውድቀቶችን እንደ የመማሪያ ዕድሎች አድርጎ መውሰድ፡፡
- ችግሮችን ለማጋራትና ምክር ለመጠየቅ ጠንካራ የድጋፍ ስርዓት ማዘጋጀት፡፡
- እንቅፋቶችን ለማለፍ እድገት ተኮር አስተሳሰብ መያዝ፡፡
ትምህርት 4. የዕድገት አስተሳሰብ ማጎልበት
ፍቺ/ትርጉም:
የዕድገት አስተሳሰብ ችሎታዎችና እውቀት በጥረት፣ ትምህርትና ጽናት አማካኝነት እያደጉ እንደሚሄዱ ማመን ነው፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- ተግዳሮቶችን መላመድና እንደ የእድገት እድሎች አድርጎ መውሰድ፡፡
- ግብረ መልስ ስለመጠየቅና ገንቢ እርምጃ ስለመውሰድ መማር፡፡
- የመሞከርና የመደጋገም ጉጉትና ፍላጎትን ማስረጽ፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- በመጻህፍት፣ ኮርሶች ወይም ምክሮች አማካኝነት መማር ላይ ማተኮር፡፡
- በራስ መተማመን እና ተነሳሽነትን ለማጎልበት በትናንሽ ድሎች መደሰት፡፡
- የተገኙ ትምህርቶችን ለመለየት የቀደመ ጊዜ ተሞክሮዎችን መግለጽ፡፡
- ለችግር አፈታት ሙከራና ፈጠራን ማበረታታት፡፡
ትምህርት 5. እርግጠኛ ባለመሆን ውስጥ ውሳኔ ማሳለፍ
ፍቺ/ትርጉም:
እርግጠኛ ባለመሆን ውስጥ ውሳኔ ማሳለፍ ያልተሟላ መረጃ ወይም የማይገመቱ ውጤቶች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ውስጥም በመረጃ የተደገፉ ምርጫዎችን መምረጥን ይይዛል፡፡
የትምህርቱ አላማዎች:
- አማራጮችን ለመገምገም እንደ የSWOT ትንተና ወይም የወጪ-ጥቅም ትንተና ያሉ ማዕቀፎችን መማር፡፡
- ስጋቶችን እና ሽልማቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ የመመዘን ችሎታን ማዳበር፡፡
- ያለው ውሱን ዳታ ቢሆንም ወቅቱን የጠበቁ ውሳኔዎች ለማሳለፍ በራስ መተማመንን ማጎልበት፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- በተቻለ መጠን ከውሳኔ በፊት የሚቻለውን ያክል ተገቢ ዳታ መሰብሰብ፡፡
- የተለያዩ ሀሳቦች ለማግኘት አማካሪዎች ወይም እኩዮችን ማነጋገር፡፡
- አማራጮችና ውጤቶችን ለማየት የውሳኔ መስጫ መሳሪያዎች መጠቀም፡፡
- የወደፊት ማስተካከያን ለማሻሻል የቀደመ ጊዜ ውሳኔዎችን መግለጽ፡፡
ትምህርት 6. የውጤታማ ግንኙነት ክህሎቶች
ፍቺ/ትርጉም:
ውጤታማ ግንኙነት ሀሳቦችን በግልጽ የማስተላለፍ፣ በንቃት የማዳመጥ እና ከሌሎች ጋር ትርጉም ያላቸው ግንኙነቶች የመፍጠር ችሎታ ነው፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- ራዕይዎን ሳቢ በሆነ መልኩ ለመግለጽ የታሪክ መንገሪያ ስልቶችን ማወቅ፡፡
- የሌሎችን ሀሳቦች ለመረዳት በንቃት የማዳመጥ ክህሎቶችን መማር፡፡
- ሀሳቦችን ለማስተጋባት ወይም አለመግባባቶችን ለመፍታት የማሳመኛ ግንኙነት ክህሎቶችን ማጎልበት፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- መልዕክትዎን ከተለያዩ አድማጮች ጋር ያስማሙ፡፡
- በቃልና የጽሁፍ ግንኙነት ላይ ግልጽትና አጭርነትን ይለማመዱ፡፡
- የመልዕክቱን መድረስ ለማሻሻል የአካል ቋንቋና የድምጽ ቃና መጠቀም፡፡
- የግንኙነት ዘይቤዎን ለማሻሻል ግብረ መልስ መጠየቅ፡፡
ትምህርት 7. ትስስርና ግንኙነትን ማጎልበት
ፍቺ/ትርጉም:
ትስስር እድሎችን ለማስፋት፣ ድጋፍ ለማግኘት እና ትብብርን ለማጠናከር ሙያዊ ግንኙነቶችን መፍጠርና ማጎልበትን ይይዛል፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- እጩ አማካሪዎችነብ፣ ባለሀብቶችን እና አጋሮችን እንዴት እንደሚቀርቡና እንደሚያሳትፉ መማር፡፡
- በመተማመን እና የጋራ ጥቅም ላይ ተመስርቶ የተረጋገጡ ግንኙነቶችን መፍጠር፡፡
- እንደ ሊንክድ ኢን ወይም የኢንዱስትሪ ዝግጅቶች ያሉ የትስስር ፕላትፎርሞችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ማጠናከር፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- ተመሳሳይ አመለካከት ካላቸው ግለሰቦች ጋር ለመገናኘት በአውደ ጥናቶች፣ ኮንፍረንሶች ወይም ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ፡፡
- ግንኙነቶችን ለማስቀጠል በመደበኝነት ክትትል ማድረግ፡፡
- እርዳታ ከመጠየቅ በፊት ለሌሎች ጥቅም መስጠት፡፡
- ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማግኘት የስራ ፈጣሪ ቡድኖች ወይም የኦንላይን ማህበረሰቦችን መቀላቀል፡፡
ትምህርት 8. ውክልናና የቡድን አመራርነት
ፍቺ/ትርጉም:
ውክልና ስራዎችን ለቡድን አባላት የመመደብ ሂደት ሲሆን የቡድን አመራር የጋራ አላማዎችን ለማሳካት ቡድኖችን መምራትና አቅማቸውን ማጎልበትን ይይዛል፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- በቡድን ጥንካሬዎች ላይ ተመስርቶ ሊመደቡ የሚችሉ ስራዎችን መለየትን መማር፡፡
- ቡድንዎን ለማነሳሳትና ለማበረታታት የአመራርነት ክህሎቶችን ማዳበር፡፡
- በቡድን ውስጥ ተጠያቂነትና መተማመንን ማጎልበት፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- ለእያንዳንዱ የቡድን አባል የስራ ድርሻዎችና ኃላፊነቶችን በግልጽ መግለጽ፡፡
- ሞራልን ለማሳደግ ገንቢ ግብረ መልስና ዕውቅና መስጠት፡፡
- ቡድንዎን ያለ ጥቃቅን ቁጥጥር ስራዎችን እንደሚፈጽም ማመን፡፡
- ሁሉም ሰው ዋጋ እንደተሰጠው እንዲሰማው የሚያደርግ የትብብር ምህዳር መፍጠር፡፡
ትምህርት 9. የግጭትና ችግር አፈታት
ፍቺ/ትርጉም:
የግጭት አፈታት አለመግባባቶችን ገንቢ በሆነ መልኩ መፍታትን የሚይዝ ሲሆን የችግር አፈታት ለችግሮች ውጤታማ መፍትሄ በመፈለግ ላይ ማተኮርን ይይዛል፡፡
የትምህርቱ ዓላማዎች:
- ግጭቶችን በሰላማዊ ሁኔታና በትብብር የመፍቻ ስልቶችን መማር፡፡
- ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት የፈጠራ የችግር አፈታት ክህሎቶችን ማዳበር፡፡
- በቡድን አባላት ወይም ባለድርሻ አካላት መካከል አለመግባባቶችን የማሸማገል ችሎታን ማጎልበት፡፡
ዋና ዋና የሚዳሰሱ ነጥቦች:
- አለመግባባት ውስጥ የገቡ ሁሉንም ወገኖች በንቃት ማዳመጥ፡፡
- ከምልክቶች ይልቅ ስረ መንስኤዎችን መለየት ላይ ማተኮር፡፡
- የተለያዩ መፍትሄዎችን ማሰላሰልና አዋጭነታቸውን መገምገም፡፡
- መፍትሄዎችን በግልጽነት መተግበርና ውጤቶቹን መቆጣጠር፡፡