ግብ መወሰን እና ራዕይን ማስማማት
ጥያቄ – የSMART ስማርት ግብ ምንድን ነው?
መልስ – የA SMART ግብ ዓላማ ተኮር፣ ሊለካ የሚችል፣ ሊሳካ የሚችል፣ ተገቢና በጊዜ የተገደበ ግብ ሲሆን ግልጽና የተግባር ኢላማዎችን ለመወሰን ይረዳል፡፡
ጥያቄ – የግል ራዕዬን ከንግድ ስራ ግቦቼ ጋር ማስማማት ያለብኝ ለምንድን ነው?
መልስ – የግል ዕሴትዎን እና የረጅም ጊዜ ህልሞችዎን ከንግድ ስራዎ ጋር ለማስማማት አላማ ተኮር እድገትና ተነሳሽነትን ያረጋግጣል፡፡
ጥያቄ – ግቦቼን በየ ምን ያክል ጊዜ መገምገም አለብኝ?
መልስ – አካሄድን ለመከታተል እና አስፈላጊ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ግቦችዎን በየወሩ ወይም በየዕሩብ ዓመቱ መገምገም ነው፡፡
የጊዜ አጠቃቀምና ቅደም ተከተል መስጠት
ጥያቄ – ጊዜ መመደብ ምንድን ነው?
መልስ – ሰዓት መመደብ በአስፈላጊ ስራዎች ላይ ያለመረበሽ ለማተኮር በቀን ውስጥ የተወሰነ ሰዓት መመደብ ነው፡፡
ጥያቄ – የትኞቹ ተግባሮች እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ ማወቅ እችላለሁ?
መልስ – አሁን፣ ቆይቶ ምን እንደሚሰራ፣ እንደሚመደብ ወይም እንደሚተው ለመወን የአስቸኳይና አስፈላጊ ማትሪክስን ይጠቀሙ፡፡
ጥያቄ – በስራ ሰዓቶች ውስጥ የሰዓት ብክነትን እንዴት ማስቀረት አለብኝ?
መልስ – የስልክ ማስታወቂያዎችን ይዝጉ፣ ቀንዎን አስቀድመው ያቅዱ፣ እንዲሁም ትኩረት ሰጥተው ለመቀጠል ሳምንታዊ የዕቅድ ማዘጋጃ መጠቀም፡፡
ዝግጁነትን እና የአእምሮ ጥንካሬን ማጎልበት
ጥያቄ – ለስራ ፈጣሪዎች ዝግጁነት ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ – ዝግጁነት እንቅፋቶችን የማለፍ፣ ለውጥን የመቀበል እና በጫና ውስጥ ወደፊት የመቀጠል ችሎታ ነው፡፡
ጥያቄ – የአእምሮ ጥንካሬን እንዴት ማጎልበት እችላለሁ?
መልስ – ትናንሽ ደረጃዎችን ይለማመዱ፣ እለትዎን ይመዝግቡ፣ ከውድቀት ይማሩ፣ እንዲሁም በዙሪያዎ ድጋፍ የሚያደርጉልዎ ሰዎች እንዲገኙ ያድርጉ፡፡
ጥያቄ – እንደ መስራች የጭንቀት ስሜት ውስጥ መግባት የተለመደ ነው?
መልስ – አዎ፡፡ ነገር ግን ጫናን በመመደብ፣ እረፍት በመውሰድ እና በመግለጽ መቆጣጠር ጠንካራና ምርታማ ሆነው እንዲቀጥሉ ይረዳዎታል፡፡
የእድገት አስተሳሰብ
ጥያቄ – የእድገት አስተሳሰብ ምንድን ነው?
መልስ – ክህሎቶች በጥረት፣ ትምህርትና ግብረ መልስ አማካኝነት እያደገ ይሄዳል ብሎ ማመን ነው፡፡
ጥያቄ – የእድገት አመለካከት የማዳብረው እንዴት ነው?
መልስ – ችግሮችን ይቀበሉ፣ ግብረ መልስ ይጠይቁ፣ አዳዲስ አቀራረቦችን ይሞክሩ እንዲሁም በመንገድዎ ላይ በትናንስ ድሎች ይደሰቱ፡፡
ጥያቄ – ከውድቀት መማር የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
መልስ – ውድቀቶች ለመሻሻል፣ ለመፍጠር እና እንደ ስራ ፈጣሪ በጥንካሬ ለማደግ የሚረዱዎትን ትምህርቶች ያስተምርዎታል፡፡
እርግጠኛ ባለመሆን ውስጥ ውሳኔ ማሳለፍ
ጥያቄ – በውሱን ዳታ ውሳኔ ለማሳለፍ ምን መሳሪያዎች ይረዳሉ?
መልስ – የSWOT ትንተና፣ የወጪ-ጥቅም ትንተና ይጠቀሙ እንዲሁም ለምርጫዎችዎ መመሪያ ለማግኘት አማካሪዎችን ያነጋግሩ፡፡
ጥያቄ – ከመወሰኔ በፊት ሁልጊዜም ምርጥ መረጃ መጠበቅ አለብኝ?
መልስ – አይ—ያለውን ዳታ በመጠቀም ውሳኔ ያሳልፉ እና እንደ አስፈላጊነቱ ለማስተካከል ዝግጁ ይሁኑ፡፡
ጥያቄ – ውሳኔ አሰጣጤን በጊዜ ሂደት ላሻሽል የምችለው እንዴት ነው?
መልስ – ያለፈ ጊዜ ውሳኔዎችን ይግለጹ፣ ምን እንደሰራ ይለዩ እንዲሁም እነዚህን ትምህርቶች በወደፊት ምርጫዎች ላይ ይተግብሩ፡፡
የግንኙነት ክህሎቶች
ጥያቄ – ታሪክ መንገር ለስራ ፈጣሪዎች የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
መልስ – ታሪክ መንገር ከደንበኞች ጋር ግንኙነት በሚያደርጉበት ወይም በሚያሳትፉበት ወቅት መልእክትዎን ተያያዥ፣ የሚታወስና ሳቢ ያደርግልዎታል፡፡
ጥያቄ – በህዝብ ፊት የመናገርና የግንኙነት ክህሎቶቼን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?
መልስ – በመደበኛነት ይለማመዱ፣ እራስዎን ይቅረጹ፣ ግብረ መልስ ያግኙ እንዲሁም በግልጽና በራስ መተማመን ይናገሩ፡፡
ጥያቄ – በንቃት ማዳመጥ ምንድን ነው?
መልስ – በንቃት ማዳመጥ ማለት ለተናጋሪው ሙሉ ትኩረት መስጠት፣ ጥያቄዎች መጠየቅ እና በአመለካከታቸው ላይ ፍላጎት ማሳየት ነው፡፡
ትስስር እና ግንኙነትን ማጎልበት
ጥያቄ – ለጀማሪዎች ትስስር የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
መልስ: ትስስር የንግድ ስራዎን ሊያሳድጉልዎ የሚችሉ አጋርነቶች፣ ምክሮች፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ድጋፍ ለማግኘት በር ይከፍታል፡፡
ጥያቄ – ከእጩ ድጋፍ አድራጊዎች ጋር ግንኙነት መመስረት የምጀምረው እንዴት ነው?
መልስ – ዝግጅቶች ላይ ይሳተፉ፣ በትህትና ይከታተሉ፣ እንዲሁም እርዳታ ከመጠየቅዎ በፊት ዋጋ/ጥቅም ይስጡ፡፡
ጥያቄ – ከትስስሬ ጋር ግንኙነቴን መቀጠል የምችለው እንዴት ነው?
መልስ – በየ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወቅታዊ መረጃዎችን በማጋራት፣ እንዴት እየሰሩ እንደሆነ በመጠየቅ ወይም እገዛ በማድረግ ግንኙነትዎን ይቀጥሉ፡፡
መመደብና የቡድን አመራር
ጥያቄ – ውጤታማ ምደባ ምንድን ነው?
መልስ: ትክክለኛ ስራዎችን በጥንካሬዎቻቸው ላይ ተመስርቶ ለትክክለኞቹ ሰዎች መመደብና ግልጽ መመሪያዎችን መስጠት ነው፡፡
ጥያቄ – በቡድኔ ውስጥ መተማመን የምገነባው እንዴት ነው?
መልስ: ግልጽ የሚጠበቁ ሁኔታዎች ያስቀምጡ፣ እውቅና ይስጡ፣ ሀቀኛ ግብረ መልስ ይስጡ እንዲሁም ጥቃቅን ቁጥጥርን ያስቀሩ፡፡
ጥያቄ – ለትናንሽ ቡድኖችም ጭምር አመራር የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
መልስ – ጠንካራ አመራር ቡድኖችን ያነሳሳል፣ አፈጻጸምን ያሻሽላል እንዲሁም አዎንታዊ የስራ ባህል ይፈጥራል፡፡
የግጭት እና ችግር አፈታት
ጥያቄ – ግጭትን ለመፍታት የመጀመሪያው ደረጃ ምንድን ነው?
መልስ – ሁሉንም ወገኖች ጣልቃ ሳይገቡ ወይም ሳይወግኑ በጥንቃቄ ማዳመጥ፡፡
ጥያቄ – የአንድን ችግር ስረ መንስኤ ማወቅ የምችለው እንዴት ነው?
መልስ – ከምልክቶቹ በስተ ጀርባ ያለውን ትክክለኛውን ጉዳይ እስከሚያውቁ ድረስ ብዙ ጊዜያት “ለምን?” ብለው ይጠይቁ፡፡
ጥያቄ – ችግሩን ከፈታሁ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ?
መልስ – መፍትሄውን በግልጽ ይግለጹ፣ በግልጽነት ይተግብሩ እንዲሁም መፍትሄው መስራቱን ለማረጋገጥ ውጤቶቹን ይከታተሉ፡፡