Course Content
የገንዘብ/ፋይናንስ አስተዳደር

የዚህ የፋይናንስ አስተዳደር ሞጁል ጠቅላላ የትምህርት ዓላማ ለውጤታማ የንግድ ስራ እንቅስቃሴ አስፈላጊ የሆኑ የዋና ዋና የገንዘብ መርሆዎችና የተግባር መሳሪያዎች መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡ ይህ ሞጁል ሲያበቃ የገንዘብ አስተዳደር መሰረታዊ ንድፈ ሀሳቦችን መረዳት፣ መሰረታዊ የበጀት ዝግጅት ስልቶችን መተግበር እና ትክክለኛ የገንዘብ ፍሰት ትንበያዎችን ማዘጋጀት፣ የተለያዩ የዋጋ ትመና ሞዴሎችን መጠቀም እና ለስትራቴጂያዊ ውሳኔዎች መረጃ ለማግኘት የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ ትንተና ማካሄድ፣ እና ሽያጮችን እና የክፍያ ሂደቶችን ለማሳደግ የሞባይል ገንዘብ ውጤቶችን ማካተትን ማጥናት ይችላሉ፡፡ ይህ አጠቃላይ አቀራረብ ግለሰቦችን በመረጃ የተደገፉ የገንዘብ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ፣ ትርፋማነታቸውን እንዲያሻሽሉ እና በአውዳቸው የስራ ውጤታማነታቸውን እንዲያሻሽሉ አቅማቸውን የማጎልበት አላማ አለው፡፡

 

ዋና ዋና የትምህርቱ ነጥቦች

  1. ስለ የገንዘብ አስተዳደር መረዳት
  2. የበጀት ዝግጅት መሰረታዊ ሀሳቦች እና የገንዘብ ፍሰት ትንበያዎች
  3. የዋጋ ትመና ሞዴሎች እና የገቢ-ወጪ ማመጣጠኛ
  4. ለሽያጮችና ክፍያዎች የሞባይል ገንዘብ ማካተት ትንተና
Scroll to Top